(ይህ የአንተ/የአንቺ ታሪክ ነው)
ከደንበኞቼ 90 በመቶ የሚሆኑት በእድሜ ትልልቅ ቢሆኑም ከእነሱ 90 በመቶ የማየው ግን ልጅነታቸውን ነው፡፡ አዋቂዎቹ ይምጡ እንጂ ከልጆቹ ጋር ነው የማወራው፡፡ የልጅነት የሆነውን ክፍል እጠይቀዋለሁ፡፡ የሚፈልገውን እጠይቀዋለሁ፡፡ በልጅነቱ ያጣውን ፍቅር፣ ትኩረት፣ መደመጥ እና መከበር እንዲያገኝ አደርጋለሁ፡፡ ከዚያ ትልቁ ሰውዬ ይድናል፤በስሜት ደህና ይሆናል ፡፡ ሂደቱ በጣም ሳይንሳዊና ዝርዝር ነው፡፡ በትምህርት፣ በስልጠና እና በልምምድ የምታገኘው እውቀት ነው፡፡ እሱን ማብራራት አልችልም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሂደቱን ዝርዝር አድርገህ ብታወራው እኛ ሀገር ችግር ነው፡፡ ሰዎች በእኔ ንግግር ብቻ የገባቸውና መንገዱ ቀላል እንደሆነ አስበው ምርመራ ሊጀምሩ ይችላሉ፤ ራሳቸው ወይም ሰው ላይ ጉዳት ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡ ጉዳዩ ግን በጣም ውስብስብ ነው፡፡ እንግዲህ አስበው አንተ እዚህ እድሜህ ላይ ሆነህ በ5 ወይም 10 ዓመትህ ላይ የገጠመህ ሕይወት ትውስታ የዛሬ ማንነትህን ሲረብሸው፣ እንቅስቃሴህን ሲገድበው፡፡
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ መንገዱን እኔን ራሴን <<ምን ምን አደረግሽ?>> ብትለኝ ሁሉንም ዘርዝሬ መናገር ያቅተኛል፡፡ ድርጊቱ እኮ ግን ተፈጽሟል፡፡ ለምሳሌ በሚሞሪ ቤዝድ ኢማጅናል ነርቸሪኒግ (Memory based imaginal nurturing child) ለምክክር የመጣችው የ30 ወይም 40 ዓመት ሴት ናት፡፡ ግን የ6 ዓመቷ ማንነቷ በእናቷ የመታቀፍ ረሃብና ጉጉት ይኖርባታል፡፡ እናቷ አሁን መጥታ እንዳታቅፋት በሕይወት የለችም፡፡ ሞታለች፡፡ ደግሞ ብትኖርም የ30 ዓመቷን ሴት መጥታ ማቀፏ ለውጥ አያመጣም፡፡ ግን ኢጎ ስቴት ቴራፒ በሚሞሪ ቤዝድ ኢማጅናል ነርቸሪኒግ (Memory based imaginal nurturing child የ6 ዓመቷ ደንበኛዬ እንድታቅፋት እናደርግና ደንበኛዬ ከገባችበት ህመም ትፈወሳለች፡፡ በአካል የሚፈፀም ምንም ነገር የለም:: በሀሳቧ እዚያ እድሜ ላይ ገብታ ድርጊቱ የተፈፀመ ያህል እንዲሰማት ነው የሚያደርገው። ደንበኛዬ የሚሰማት ግን በሀሳብ እንደሆነ ሳይሆን በተግባር፤ አሁን በአካል እየተፈፀመ እንዳለ ነው። ይህ <<እግዚአብሔር ለሰዎች የሰጠው ጥበብ ነው>> ነው የምንለው.......።
ትዕግሥት ዋልተንጉሥ
ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ
ገፅ 131
Comments