የብዙ ነገዶች ማኅበረሰብ
ከደራሲ ዶናልድ ሌቪን
ትርጉም አቶ ሚሊዮን ነቅንቅ
አዲስ አበባ 2007 ዓ .ም. ታተመ
የአንድን ማኅበረስብ ድንበሮችና በየክፍሉ መሃል በስፋትም ሆነ በዓይነት የአለውን አመዳደብ ከመደንገግ ባሻገር: ጠቅላላው የአወቃቀር ባሕርዩ እንዴት እንደሚሰራ መረዳትና ክፍሎቹም እርስ በርሳቸው እንዴት እንደሚዛመዱ መታወቅ አለበት:: ምንም እንኳን በማንኛውም ማኅበረሰብ ሰዎችና ሚናዎች በብዙ መንገድ የሚገናኙ ቢሆንም እያንዳንዱ የማኅበረሰብ ሥርዓት በልምድ የተቀበለውና አባላቱ በተለያየ መልክ ደጋግመው ለማድረግ የሚጥሩለት ግል ዓቀፍና ቡድን አቀፍ ግንኙነቶችን የማዋቀር የራሱ ልዩ ልዩ መንገድ አለው::
እንደዚህ ያለውን ሐረግ ወይም ሥርዓት በሐሳብ ለመቅረፅ ጠቃሚው ዘዴ ግለሰቦችን እርስ በርሳቸው ሊገናኙ የሚችሉበትን ሁለት አቅጣጫዎች ማስታወስ ያስፈልጋል:: እነዚህም አቅጣጫዎች: ቋሚ አቅጣጫ እና አግዳሚ አቅጣጫ ይሰኛሉ:: የመጀመሪያው ሰበብ ማለት ላዕላይ አቅጣጫ ስዎችን በሥልጣን በኅይልና በክብር ደረጃቸው ይለያቸዋል:: ደረጃው ከፍተኛ ሆኖ የግንኙነት ዓይነት ማክበርና ትእዛዝ መፈፀም የተጫነው እንደሆን በደረጃ የማበላለጥ ስርዓት ወይም እርከናዊ ስርዓት ይባላል ላዕላይ ደረጃ ተቀናንሶ. . . .
ከመፅሃፉ የተወሰደ
Commentaires