በመርስዔ ኃዘን ወልደ ቂርቆስ
በእንጦጦ ዳገት የባቡር መንገድ ስለመሰራቱ
የባቡር መንገድ ስራ አዲስ አበባ ላይ የተጀመረው በ1894ዓ.ም ነው፡፡ በእንጦጦ ዳገት ላይ ግን የባቡር መንገድ የተሠራው በ1897 ዓ.ም ነው፡፡ መንገድ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በእንጦጦ ዳገት ላይ እየተጥመዘመዘ እስከ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ድረስ በመሀንዲሱ በሙሴ ካስተኛ ተቀየሰና ዳገቱ እየተቆፈረ ተደለደለ፡፡ ከዚያም በኃላ ድንጋይ እየተነጠፈበትና ኮረት እየተሞላበት ለባቡር ማስኬጃ እንደሚስማማ ሆኖ ተዘጋጀ፡፡
ሠራተኞቹ ገንዘብ የሚከፈላቸው የቀን ሠራተኞቹ ሲሆኑ፣ ወር ተረኛ የሚባለውም ወታደር በጉልበቱ አገለገለ፡፡ የቀን ሠራተኞቹም ጉራጌዎች ናቸው፡፡ በዚያ “ያ ወነቦ፣ ዘበኛ ይሰጥሽ ዳቦ” እያሉ ግጥም እየገጠሙ ያዘፍኑ ስለነበረ ነው፡፡ የሚቆፍሩበትንም መሳሪያ “ወነቶ” ይሉት ነበር፡፡
#የሐያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ፡
በመርስዔ ኃዘን ወልደ ቂርቆስ
ከመጽሓፉ የተወሰደ
Comments