ስንዱ አበበ
ድንገት ትዝ አልሽኝ፡፡ ለምን? ካልሺኝ ለምን ጠየቅሽኝ ስለምልሽ ዝም በይ፡፡ ይልቁንስ…….
ሳራዬ! ዛሬ ብታይ በጣም ነው ስበሳጭ የዋልኩት፡፡ እንደዚህ ማለት አይቻልም እንጂ እንዲያውም እንዲህ ብለው ጥሩ ነበር፡- እኔ ዛሬ ሞቼ፣ እኔው ዘንድ ለቅሶ ደርስኩና እራሴን ሳስተዛዝን ነው የዋልኩት፡፡ ምን ሆነህ ሞትክ ትይኝ ይሆናል፡፡
ይቺ ልጅ እኮ ዛሬ ቀጥራኝ ቀረች፡፡
አሁንም የቷ ልጅ? ትይኝ ይሆናል፡፡
ያቺ ከትናንት በስቲያ የተዋወቅኳት ልጅ
የት ነው? የተዋወቅካት ትይኝ ይሆናል፡፡
እዚያ አንድ የማህበር ጠበል ቢጤ ቤት ሄጄ በጠላውና በሷ ጨዋታ ስጠመቅልሽ ውዬ…….
ሳርዬ ብታያት መቼም ምነው ወንድ በሆንኩ ማለትሽ አይቀርም ነበር……
ታዲያ ምን ያረጋል ቀጥራሽ ትጠፋለች፡፡
እኔ ደግሞ ብታይ ሰሞኑን ዝም ብሎ ሆድ ይብሰኛል፡፡
“እንኳን አኮፋዳዬን ቀምተውኝ እንደው አልቅስ አልቅስ ይለኛል” አለ አሉ ለማኝ፡፡
ግን ለምንድን ነው ሳርዬ እናንተ ሴቶች እኛን ቀጥራችሁ የምትጠፉት?
ደሞ እኮ ብታያት አትጠግቢያትም፡፡ ዝምብለሽ አይን አይኗን ብታዩ አይን አይንሽን ደስ ይልሻል፡፡ የአንቺም አይንኮ እንደዚሁ ነው፡፡ ዝም ብለው ያዩት እንደሆነ ዝም ብሎ ደስ ይላል፡፡ የድምጽ ነገርም ነገር አለው፡፡ ልክ እንዳንቺ ባይሆንም አንድ ሁለት ቀን ብትገናኙ ያንቺን ሳይበልጥ አይቀርም፡፡ በተረፈ ምን እያልኩሽ ነበር! አዎ! ልጅቷ ቀጥራኝ ጥፍት አለች፡፡
ታዲያ እኔ ወንድምሽ ደሞ አንበሳ አይደለሁ ድውል አረኩላት፡፡
አነሳች፡፡
ሀሎ!
ሀሎ!
ሀይ!
አለን!
ታዲያስ
አለን!
ምነው?
ምኑ?
ለምን ቀረሽ?
“ውይይ”
ግን ምን ሆነሽ ቀረሽ?
ብታይ አንድ ጓደኛዬ መጥታ…..
ከየት?
ከክፍለ ሀገር….እና ከሷ ጋር……
አያይ ምንም አይደል……….
“ብታይ እኔ ደሞ በጣም አሰብኩ”
ግድ የለም …..ታዲያ መች እንገናኝ?
ነገ ይመችኃል?
በ….ይሁን …እሺ….ቻው
ሳርዬ ይብቃኝ፡፡
የኔ ማስታወሻ - ስንዱ አበበ
ከመጽሃፉ የተወሰደ Senedu Abebe (Senedu Abebe)
Kommentare