በፍቅረማርቆስ ደስታ
"የኔነት ስሜት በአንድ ወገን፣ የእኛነት ስሜት በሌላ በኩል እንደምሶሶ ተራርቆ የተተከለበት መሬት አሁንም ስቃይዋን ለመቀነስና ዕድሜዋን ለማርዘም፣ ቀሪ ውበቷን እንደያዘች እንድትቆይ ለማድረግ አልተቻለም።
"ሁለት የሚንቆራቆሱ ሐሳቦች ቢኖሩም አንዱ ሌላውን አይሰማም፣ መስማትም አይፈልግም። ችግሩ ሃላፊነትን የመቀበልና ያለመቀበል ጥያቄ ነው፤ ችግሩ የበቃኝ አልበቃኝ ጥያቄ ነው፤ ችግሩ ችግሩን ያለማወቅ ጥያቄ ነው…ችግሩ የመቻቻል ያለመቻቻል ጥያቄ ነው። መደማመጥ የሌለበት፣ ለነገው ትውልድ የማይታሰብበት የሆዳም ዘመን መሆኑ ነው - ግዙፍ መሰናክል።
"ትናንት አንዱ ሌላውን አይናችሁን ጨፍኑ እያለ አሞኘ፣ ዘረፈ፣ በመሣሪያ የበላይነት እየገደለ በሃብት ደለበ። ዛሬ ደግሞ በረጅ ዕጁ፣ በምላሱ፣ በግንባር መጋፈጡን ትቶ አንዱን ከሌላው ጋር እያባላ በህፃናት፣ በአዛውንቶች…እልቂትና ሰቆቃ እየተዝናና እያላመጠ ይጎነጫል።…"
"የዘርሲዎች ፍቅር"
በፍቅረማርቆስ ደስታ
Comments